የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ ክቡር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የሰጡት ሳምንታዊ የፕሬስ መግለጫ ====================


May be an image of 1 person and standingየኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ ክቡር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የሰጡት ሳምንታዊ የፕሬስ መግለጫ

====================
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ ክቡር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ፤ መጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም ለመገናኛ ብዙኃን ሳምንታዊ የፕሬስ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸው የፖለቲካ ዲፕሎማሲ፣ የትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ፣ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ እንዲሁም የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲን የተመለከቱ ጉዳዮችን ዳስሰዋል።
1.ከፖለቲካ ዲፕሎማሲ አኳያ ፡-
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን-
• በሱዳንና ደቡብ ሱዳን የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ የተመራ ልዑካን ቡድን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል ፡፡ የውሃው 86% አመንጪና ከህዝቧ 60% መብራት አልባ የሆነች አገር ከድህነት ለመውጣት እየሰራች ያለ ፕሮጄክት እንጂ ታችኞቹን አገሮች ለመጉዳት ምንም ፍላጎት የሌለት መሆኑን ፣የውሃ ሙሌት የግንባታው አካል መሆኑን፣ የሶስትዮሽ ድርድር በአፍሪካ ኅብረት አማካኝነት እንዲቀጥል ፍላጎት መሆኑን ማብራራታቸው፡፡ የተጀመረው ድርድር የማይሳካ ከሆነ በመርሆች መግለጫ(DOP) መፍትሔ ማግኘት እንዳለበት ተገልጾላቸዋል፡፡ ኢትዮጵያ በቀጠናው በሚትጫወተው ሚና አንጻር፣ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ግንኙነት ተጠናክሮ መቀጠል አስፈላጊ መሆኑን የቡድኑ መሪ መግለጻቸውን፣
• በኒውዮርክ የኢ.ፌዲ..ሪ. የተመድ ቋሚ መልዕክተኛ ጽ/ቤት ለአፍሪካ አገራት አምባሳደሮች በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ገለጻ መሰጠታቸው፣
• በተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት የአፍሪካ ተወካይ ከሆኑት ከኒጀር እና ቱንዝያ አምባሳደሮች ጋር የትግራይ ክልል ወቅረታዊ ጉዳይ አስመልክቶ ውይይት መካሄዱ፣
• በሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጋር በአገራችን ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት መደረጉን፣
• የአውሮፓ ህብረት እና አውሮፓ አባል አገሮች ቤልጅየም ፣ፈረንሳይ ፣ኦስትሪ ፣የአውሮፓ ህበረት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በትግራይ ክልል ያለው ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ መስጠታቸው፤
• በሴኔት ከውጭ ግንኙነት ኮሚቴ አባላት መካከል ከተወሰኑ ሴናተሮች ጋር በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ጉዳይ አስመለክቶ ገለጻ መሰጠቱ፣
• ክቡር አቶ አህመዴ ሽዴ ከአውሮፓ አለም አቀፍ አጋሪነት፣የአውሮፓ ህብረት ቀውስ ጉዳይ እና የአውሮፓ ህብረት ሰብአዊ መብት ኮሚሽነሮች ጋር በብራሴልስ ውይይት ማድረጋቸው፤ ፡፡ የህብረቱ የስራ ሃላፊዎች በትግራይ ክልል ያልተገደበ የሰብአዊ ዕርደታ እንዲደርስና የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲጣራ መንግስት ለወሰደው እርምጃ እውቅና እንደሚሰጡ መናገራቸው፣
• በእስራኤል ኤምባሲያችን በእየሩሳሌም ከተማ ከሚገኘው ፖሊሲ ጥናት ተቋም ጋር በመተባበር “ከኢትዮጵያ ወደ ኢየሩሳለም “ በሚል ርዕስ በተለይም በእየሩሳለም ያሉትን ገዳምና ጥንታዊ ህንጻች ላይ ያተኮረ ውይይት መካሄዱ፣
• ከኤርትራ ጋር ያለው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ፍላጎቶች መሆኖሩን በማንሳት ፤ የጎረቤት አገሮች በኢኮኖሚ መተሳሰሩ ፋይዳው የጎላ መሆኑን መጥቀሳቸው፣
2.በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ፤
• የሰብአዊ መብት ጥሰትን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከተመድ አካላት ጋር ተባብሮ ለመሥራት መግባባት ላይ መደረሱ፣
• የኤርትራ ወታደሮች ከድንበራችን አከባቢ እንዲወጣ ከስምምነት ላይ መደረሱን ፤ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአስመራ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት መገለጹ ፣
• ጽንፈኛው የህወሃት ቡድን ሽንፈት በሚገባ ካለመረዳት፤ የተወሰኑ ቡድኖች የተኩስ አቁም ስምምነት የሚሉ ጥሪዎች ተቀባይነት የሌላቸው መሆኑን፤ መንግስት የቡድኑ አባላት እጅ እንዲሰጡ ያቀረበው የጊዜ ገደብ ማለቁን፤
• የተመድ የሰብአዊ ድጋፍ ሰጭ ድርጅቶች በትግራይ ያለው ሁኔታ እየተሻሻለ መሆኑን በማንሳት የኢትዮጵያ መንግሰት ሊመሰገን እንደሚገባ ጠቅሰው ፤ ነገር ግን የእርዳታ ተደራሽነት ሊረጋገጥ እንደሚገባ መጠየቃቸው፡፡
3. ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣
• በግብፅና በሱዳን በኩል የህዳሴ ግድብ ድርድር ወደ ጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ለመውሰድ የሚደረጉ ጥረቶች ተገቢነት የሌላቸው መሆኑን፤ የአፍሪካ ህብረት ድርድር መለወጥ ካስፈለገም እ.ኤ.አ. በ2015 በተፈረመው የመርሆች መግለጫ( DOP) መሰረት መፍትሔ መፈለግ እንዳለበት ፤
• የህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ ያለውን ፋይዳ ለተቀረው ዓለም ለማስረዳት በእንግሊዝኛና በአረብኛ ቪድዮች ተዘጋጅተው በታዋቂ ሰዎች በአትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ እና በተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ኡመር ኢዲሪስ አማካኝነት መልዕክቶች መተላለፋቸው፡፡ እንዲሁም ስለ ህዳሴ ግድብ አስመልክቶ በፈረሳይኛ ቋንቋ የተዘጋጁ አጭር ቪድዮ ተዘጋጅቶ መልዕክት መተላለፉ ፤
• በካናዳና አሜሪካ ያሉ ኤምባሲዎቻችን በህዳሴ ግድብ ላይ ያተኮረ ውይይት በበይነ መረብ ማካሄዳቸው፣
4.የኢትዮ -ሱዳን ድንበር ጉዳይ በተመለከተ፣
• እንደ ተባበሩት አረብ ኤምሬት ያሉ በርካታ አገሮች በኢትዮ-ሱዳን መካከል ያለውን የድንበር ችግሮችን ለመፍታት እየተጫወቱት ያለው በጎ ሚና እውቅና የሚሰጠው መሆኑን፣
• የሱዳን ህዝብ በታለቁ የኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ከመንግሰቱ ጋር ተመሳሳይ አቋም የሌለው መሆኑ እና ጠቀሜታውን እንደሚረዳ መረጃዎች መኖሩ ፣
• ከሱዳን ጋር ያለውን የድንበር ውዝግብ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ኢትዮጵያ የያዘችውን አቋሚ አለም አቀፍ ማህበረሰብ በአዎንታ የሚመለከተው መሆኑ፣ ኢትዮጵያ ውይይት እንደሚታስቀድም ፡፡
5.ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ በተመለከተ ፤
• 4 የደቡብ አፍሪካ የኩባንያ ሥራ ኃላፊዎች በአገራችን የቢዝነስ ጉብኝት ማድረጋቸው ፡፡ ኩባንያዎቹም በማዕድን ፣በዘመናዊ ግብርና፣ በጨርቃ ጨርቅ፣በፔትሮኬሚካል ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ማሳየታቸው፣
• በዶሃ ኤምባሲ ኮን ግሩፕ ከተባለ ድርጅት ጋር በመተባበር በማኑፋክቸርንግ፣በግብርና ፣ማዕድንና ቱሪዝም ዙሪያ በበይነ መረብ የኢንቬስትመንት ማስተዋወቅ ሥራ መሥራቱን እና በ8ኛው አለም አቀፍ የግብርና ንግድ ትርዒት መሳተፉ፡፣
• ዱባይ ንግድ ምክር ቤት የውጭ ጉዳዮች ዳይሬክተር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር የንግድ ምክር ቤት አባላቸው በኢንቬስትመንትና በንግድ ዙሪያ እንዲሰማሩ እና ከአገራችን አቻ ማህበራት ጋር ተባብሮ ለመሥራት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን መጥቀሳቸው፤
• በአልጀሪስ ኤምባሲ ለቡና ኢምፖርተሮችና ለኢትዮጵያወያን ቡና ላክዎች በበይነ መረብ የውይይት መድረክ መካሄዱ፣
6. ዜጋ ተኮርና ዳያስፖራ ዲፕሎማሲ
• በውጭ አገር በችግር ላይ የሚገኙ 906 ዜጎች ከሳውዲ አረቢያ ጂዳና ሪያድ ከተሞች ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፣
• በአሜሪካ በሲያትል አሜሪካዊ ኤሪትራውያን እና ኢትዮጵያውያን ህወሃት በሀገር መከላከያ የፈጸመን ፣የቡድኑ ደጋፊዎች የሀሰት መረጃ በመቃወም እና የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጰያ በሚመለከት ጉዳይ ላይ የሚወስዳቸው ውሳኔ እንዲጤን የሚጠይቁ ሰልፍ መካሄዱ ፡፡ እንዲሁም ተመሳሳይ ሰልፎች በዋሽንግተን እና ሳን ፍራንስኮ መካሄዳቸውን ፡፡ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዳይስፖራው ለአገሩ እሳየ ያለውን ከፍተኛ ድጋፍ እውቅና የሚሰጠው መሆኑን መገለጹ፤
7.የአቅም ግንባታ
• የቆንስላ አገልግሎትን በኤሌክትሮኒክስ አገልግሎት ለመስጠት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የለማ ሶፍትዌር እና ፎረንስክ ምርመራ ጋር ተያያዞ ሰነድ ለሚረጋግጡ ሰራተኞች ስልጠና መሰጠቱ፣
• በውጭ አገር የስራ ዕድል ፈጠራ እና በቱሪዝም ብራንድ “ ምድረ ቀደምት ”ዙሪያ ለአምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ስልጠና መሰጠቱ፤Back to Home

More News ..

Press Briefing Summary Read More


Weekly press briefing of MFA Read More


የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ ክቡር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የሰጡት ሳምንታዊ የፕሬስ መግለጫ ==================== Read More


H.E Deputy Prime Minister and Foreign Minister Demeke Mekonnen delivered a Statement at the 46th Session the United Nations Human Rights Council today a few minutes ago. Read More


Press Statement on #Ethiopia-#Sudan Border ============ Read More


Electricity a must Read More


Deputy Prime Minister and Minister for Foreign Affairs of Ethiopia Demeke Mekonnen calls for increased #Indian investment in #Ethiopia Read More


Facts on the #Ethiopia -#Sudan Boundary Issue Read More


Deputy Prime Minister and Minister of Foreign Affairs of #Ethiopia Demeke Mekonnen confers with Foreign Minister of #Turkey Mevlüt Çavuşoğlu Read More


የጅቡቲ ልዑካን በአዲስ አበባ የተገነቡ ፓርኮችን ጎበኙ Read More


Read More News...

VISITOR COUNT
TODAY COUNT:   10
THIS WEEK:   371
THIS MONTH:   1824
THIS YEAR:   13273
TOTAL:    18068
         Services
      * Visa Service
      * Document Authentication
      * For Diplomatic Community
      * For Bussiness Community
      * Government E-Services
         Media
      * Week in the Horn
      * Press Release
      * Speech
      * Articles

Subscribe Our News Posts